
እሑድ 4 ኦክቶበር 2026 ጥዋት 6:16:57
የኤርትራ ሠራዊት ድንበር ተሻግሮ ባለፉት ቀናት በተካሄዱ ውጊያዎች ውስጥ መሳተፉን በመግለጽ የኢትዮጵያ ምላሽ ከባድ እንደሚሆን ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣን ተናገሩ። ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ ኒውክሌር ኃይል ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ሆነው የተሾሙት አብረሃም በላይ (ዶ/ር) የኤርትራ መንግሥት ጦር በጦርነቱ በቀጥታ መሣተፉን በመጥቀስ “እጁን እያስገባ የማያርፍ አካል ካለ ምላሹ ምን እንደሆነ በጣም ግልጽ ነው” ብለዋል።

__
የሁቲ አማፂያን በሳዑዲ አረቢያ ዋና ከተማ ሪያድ የሚገኘውን የነዳጅ ማከማቻ በተወንጫፊ ሚሳዔል እና ድሮኖች ማጥቃታቸውን አስታወቁ። ሳዑዲ አረቢያ ጥቃቱ ስለመፈጸሙ ወዲያውኑ ማረጋገጫ አልሰጠችም። የሁቲ ታጣቂዎች ጥቃቱን የፈጸሙት ሳዑዲ በሰነዓ እና ሌሎች የየመን ግዛቶች ላይ ለፈጸመቻቸው የአየር ድብደባዎች ምላሽ መሆኑን ተናግረዋል።

ቅዳሜ 3 ኦክቶበር 2026 ጥዋት 10:19:13
የህወሓት ኃይሎች መዲናዋን ለቅቀው መውጣታቸውን የክልሉን ጋዜጠኛ እና ነዋሪዎችን ጠቅሶ የፈረንሳይ የዜና ወኪል (ኤኤፍፒ) ዘገበ። ከፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ጋር በመሆን ከትግራይ ኃይሎች ጋር እየተዋጋ ያለው ‘የትግራይ የሰላም ኃይሎች’ በበኩሉ የክልሉን ዋነኛ አውሮፕላን ማረፊያ መቆጣጠሩን መግለጹን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።

ቅዳሜ 3 ኦክቶበር 2026 ጥዋት 4:56:14
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ እንደገና የዲፕሎማሲ ግንኙነታቸውን አቋርጠዋል። ይህ የቅርብ ጊዜ የዲፕሎማሲ ስብራት በሁለቱ አገራት መካከል ለአስርት ዓመታት የቆየውን ተለዋዋጭ ግንኙነት እንደገና ወደ ፊት አምጥቷል። ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ባለፉት 36 ዓመታት ውስጥ ከቅርብ ወዳጅነት እና ትብብር እስከ ጦርነት፣ ከዚያም ወደ ረዥም የዲፕሎማሲ መራራቅና “ጦርነትም ሰላምም የሌለበት” ሁኔታ የደረሱ ሲሆን፣ በኋላም ዕርቅና የግንኙነት መሻሻል አሳይተዋል።

ዓርብ 2 ኦክቶበር 2026 ጥዋት 10:29:41
የህወሓት ሊቀ መንበር የሆኑት ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ በተለያዩ ቦታዎች አዲስ ጦርነት መጀመሩን ተናግረዋል። የትግራይ ሕዝብ “የፖለቲካ ልዩነቶቹን ወደ ጎን ትቶ ለኅልውናው እንዲቆምም” አሳስበዋል። ደብረፅዮን ትናንት መስከረም 21/2019 ዓ. ም. በሰጡት መግለጫ፤ በውጊያው ያለውን ወታደራዊ ሁኔታ ሲያብራሩ የትግራይ ጦር “በተለያዩ አካባቢዎች እየተዋጋ መሆኑን” ገልጸዋል።

ዓርብ 2 ኦክቶበር 2026 ጥዋት 5:26:05
ኢትዮጵያ በኤርትራ መዲና አሥመራ የሚገኘውን ኤምባሲዋን ለመዝጋት መወሰኗን እና 10 የኤርትራ ዲፕሎማቶች ከአገሪቱ እንዲለቁ ትዕዛዝ መስጠቷን ተከትሎ፤ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ሁሉንም የዲፕሎማሲ ግንኙነቶች ማቋረጧን አስታወቀች። ኢትዮጵያ ኤርትራን “በጠብ ጫሪነት እና የትንኮሳ” ድርጊቶች ስትከስ ኤርትራ በምላሹ፤ ኢትዮጵያ “እነዚህን ያልተገቡ የጠብ አጫሪነት ድርጊቶች ምክንያታዊ ለማድረግ ኤርትራን ከስሳለች” ብላለች።

ዓርብ 2 ኦክቶበር 2026 ጥዋት 4:54:01
ኢትዮጵያ የግብፅ ዲፕሎማት አሕመድ ሞሐራን አሕመድ ሶሊማን በ48 ሰዓታት ውስጥ ከአገር እንዲወጡ ስትወስን ግብፅ በበኩሏ የአጸፋ እርምጃ መውሰዷን አስታውቃለች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ዲፕሎማቱ ከአገር እንዲወጡ የተወሰነው “ዲፕሎማሲያዊ ጥሰት” በመፈጸማቸው መሆኑን አመልክቷል። ግብፅም በካይሮ ያሉት የኢትዮጵያ ዲፕሎማት በ48 ሰዓታት ውስጥ ከአገር እንዲወጡ አሳስባለች።

ሰኞ 21 ሴፕቴምበር 2026 ጥዋት 10:28:55
ሰባት ታጣቂ ቡድኖች “ትብብር ለኅልውና” የተሰኘ ጥምረት መመሥረታቸውን እሁድ መስከረም 10/2019 ዓ.ም. አስታውቀዋል። ይህንን ትብብር ከመሠረቱት የትጥቅ ቡድኖች መካከል የተወሰኑት በአንድ ወቅት በጠላትነት የሚተያዩ እና እርስ በርስ የተዋጉ ነበሩ። እነዚህ ትብብር መሥርተናል የሚሉት ታጣቂ ቡድኖች ባለፉት ዓመታት በጠላትነት የሚተያዩ አንዳንድ ጊዜም ግጭት ውስጥ የገቡ ነበሩ። ቡድኖቹን ምን አንድ ያደርጋቸዋል? በምንስ ይለያያሉ?

ሐሙስ 24 ሴፕቴምበር 2026 ጥዋት 10:20:31
የትግራይ የእርስ በርስ ጦርነት በፕሪቶርያ ስምምነት ከተገታ ወዲህ ከረቡዕ መስከረም 13 አንስቶ ግጭት በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግመኛ ተቀስቅሷል። ረቡዕ ዕለት ግጭቱ ስለ መጀመሩ ይፋዊ መረጃ ቢወጣም ማክሰኞ ዕለት በትግራይ አላማጣ ከተማ ተከታታይ የድሮን እና የአውሮፕላን ጥቃቶች መፈጸማቸው ተዘግቧል። ግጭቱ ይፋ መሆኑን ተከትሎ የተለያዩ ወገኖች አቋማቸውን እያንጸባረቁ ነው። ስለ ግጭቱ አስካሁን የምናውቀው ምንድን ነው?

ረቡዕ 23 ሴፕቴምበር 2026 ከሰዓት 12:03:26
ለወራት በውጥረት ውስጥ በቆየው የትግራይ ክልል ውስጥ ግጭት መቀስቀሱን የህወሓት እና የፌደራል መንግሥቱ ባለሥልጣናት ገለጹ። በትግራይ ኃይሎች እና በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት መካከል ጦርነት መቀስቀሱ የተገለጸው ረቡዕ መስከረም 13/2019 ዓ. ም. ማለዳ የትግራይ ኃይሎች መቀለ የሚገኘውን አውሮፕላን ማረፊያ ተቆጣጥረው በረራዎች መቋረጣቸው ከተነገረ በኋላ ነው።

ረቡዕ 23 ሴፕቴምበር 2026 ጥዋት 7:36:10
የትግራይ ኃይሎች ዛሬ ማለዳ በክልሉ ዋና ከተማ መቀለ የሚገኘውን አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያን መቆጣጠራቸው ከተሰማ በኋላ ወደ ትግራይ በረራዎች ተቋረጡ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ ረቡዕ ረፋድ ላይ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ በትግራይ ክልል የሚያደርገውን በረራ “ለጊዜው መቋረጡን” አስታውቋል።

ረቡዕ 23 ሴፕቴምበር 2026 ጥዋት 3:55:48
ባለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ላይ በርካታ ኃይሎች በአንድ የሚያስተሳስሯቸውን ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ትስስሮችን ፈጥረው ተንቀሳቅሰዋል። ከእነዚህም መካከል አገሪቱን በአዲስ መልክ ያዋቀረው እና ለረዥም ጊዜ ያስተዳደረው ኢሕአዴግ እና ከተቃዋሚዎች መካከል የበርካቶችን ድጋፍ አግኝቶ የነበረው ቅንጅት ተጠቃሾች ናቸው። እነዚህ እና ሌሎች ባለፉት አሥርታት የታዩ ስብስቦች ለምን ተመሠረቱ? ምንስ አስገኙ? ፍጻሜያቸውስ ምን ሆነ?

ማክሰኞ 22 ሴፕቴምበር 2026 ጥዋት 3:59:08
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራውን መንግሥት ከሥልጣን ማስወገድ ዓላማው ያደረገ ነው የተበላው “ትብብር ለኅልውና” የተሰኘ ጥምረት መመሥረቱ ይፋ ሆኗል። ይህ ስብስብ በኢትዮጵያ የብሔር ፖለቲካ ውስጥ አንጋፋ ከሆኑት ጀምሮ ዓመታት የሚቆጠር ታሪክ ያላቸው ቡድኖች፣ እንዲሁም በጠላትነት ይተያዩ የነበሩ ቡድኖች ያሉበት ነው። በትግራይ፣ በአማራ፣ በአፋር፣ በኦሮሚያ፣ በሶማሊ እና በቤኒሻንጉል ክልሎች ውስጥ መሠረታቸውን ያደረጉት እነዚህ ታጣቂ ቡድኖች ታሪካዊ ዳራ ምን ይመስላል?

ሐሙስ 24 ሴፕቴምበር 2026 ጥዋት 3:59:48
አቶ ልደቱ አያሌው እና አቶ ጃዋር መሐመድ በሰባት ታጣቂ ኃይሎች የተመሠረተውን ፀረ-መንግሥት ትብብር በተመለከተ የተለያየ አቋም አላቸው። ሁለቱም ፖለቲከኞች የትብብሩን ምሥረታ አስፈላጊነት በተለያየ አገላለፅ ቢያምኑበትም በሂደቱ፣ በትብብሩ አባላት የእርስ በርስ ግንኙነት እና በቀጣይ ውጤቱ ላይ ግን ልዩነቶችን አንፀባርቀዋል። ቢቢሲ ሁለቱን ፖለቲከኞች ትብብሩን በተመለከተ አስተያየታቸውን እንዲሰጡት ጠይቋል የጠይቋቸዋል።

ሐሙስ 17 ሴፕቴምበር 2026 ጥዋት 10:00:05
ኤርትራ ነጻ አገር ከሆነች ጀምሮ እየመሯት የሚገኙት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ፤ የፖለቲካ ለውጦችን እንዲያካሂዱ በይፋ ጥያቄ ያቀረቡት ከፍተኛ ባለሥልጣናትን በቁጥጥር ስር አውለዋው ደብዛቸው ከጠፋ 25 ዓመታት ተቆጥረዋል። ቡድን 15 የሚባሉት ባለሥልጣናት ያቀረቡት ጥያቄ ምን ነበረ? ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ለሩብ ክፍለ ዘመን ያሉበት ስላልታወቁ የትግል ጓዶቻቸው ምን ይላሉ?

ረቡዕ 16 ሴፕቴምበር 2026 ጥዋት 3:58:57
በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ውስጥ በሴቶች እና በሕጻናት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች፣ አሰቃቂ ግፎች እና ግድያዎች ከፍተኛ ትኩረትን እየሳቡ በየጊዜው መነጋጋሪያ ሆነው ሲያልፉ ቆይተዋል። ከእነዚህ በሕዝቡ ውስጥ ቁጣን ከቀሰቀሱ ጥቃቶች ጋር በተያያዘ እየተነሳ ያለው ጥያቄ ወንጀሉን የፈጸሙ ሰዎች ተገቢውን ቅጣት አግኝተዋል ወይ የሚለው ነው? ነገር ግን በተለይ ከፍተኛ ትኩረትን ስበው የነበሩ የጥቃት እና የግድያ ወንጀሎች መቋጫቸው ምን እንደሆነ ሳይታወቅ ተድበስብስው መቅረታቸው ወይም ፈጻሚዎቹ ነጻ የሚሆኑበት አጋጣሚዎች ታይተዋል።

ቅዳሜ 12 ሴፕቴምበር 2026 ጥዋት 4:52:11
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ታጣቂዎች ፈጸሙት በተባለ ጥቃት ከዘጠኝ ያላነሱ ነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪዎች ሙሉ በሙሉ እና በከፊል መቃጠላቸውን ቢቢሲ ከምንጮች እና የሳተላይት መረጃዎችን በማመሳከር አረጋግጧል። በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ከተጋሩ ቪዲዮዎች በመነሳት ቢቢሲ የሳተላይት ምሥሎችን በመጠቀም ጥቃቱ ስለተፈጸመበት ስፍራ ዝርዝር መረጃን ለማግኘት ችሏል። በተጨማሪም ክስተቱን በሚመለከት መረጃ ያላቸውን እና የአካባቢው ነዋሪዎችን በማናገር ስለጥቃቱ ዝርዝር መረጃን አግኝቷል።

ዓርብ 28 ኦገስት 2026 ጥዋት 4:02:39
አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ወታደራዊ ዘመቻ ከጀመሩ ከስድስት ወራት በኋላ፣ አጭር ይሆናል ተብሎ የተጠበቀው ጦርነት፣ መጨረሻው ግልጽ ያልሆነ እና የተራዘመ ሆኗል። የካቲት 21/2018 ዓ.ም. እስራኤል እና አሜሪካ በኢራን ላይ ጦርነቱን ሲጀምሩ በሳምንታት ውስጥ እንደሚቋጭ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ገልጸው ነበር። ነገር ግን ጦርነቱ ጋብ እያለ አስካሁን ዘልቆ ተጽእኖው በዓለም ዙሪያ እየተሰማ ነው። በጦርነቱ ምክንያት ባለፉት ስድስት ወራት ማን ከፍተኛውን ዋጋ ከፈለ?

ማክሰኞ 18 ኦገስት 2026 ጥዋት 4:03:51
ቱርክ፣ ሳዑዲ አረቢያ እና ፓኪስታን ‘የመካ ስምምነት’ን ከፈረሙ ከአንድ ሳምንት በላይ ሆኗቸዋል። አንዳንድ ተንታኞች አገራቱ የተፈራረሙትን የመከላከያ ስምምነት “የሱኒ ስምምነት” ወይም “የሙስሊም ኔቶ” ሲሉ ጠርተውታል።

ሰኞ 29 ጁን 2026 ጥዋት 3:58:53
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር ባላት ግንኙነት የተነሳ የኢራን ዋነኛ ዒላማ ከሆነች በኋላ በቀጣናው አገራት ላይ ያላት መተማመን እየቀነሰች ነው። ለፖለቲካ፣ ለምጣኔ ሃብት እና ሌሎች ፍላጎቷን ለማሟላት ከቀጣናው ውጭ መመልከትን መርጣለች። ለዚህም ከሕንድ፣ ከዩክሬን፣ ከግሪክ፣ ከቆጵሮስ እና ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትስስር እያጠናከረች ነው።

ረቡዕ 11 ማርች 2026 ጥዋት 12:00:00
አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት መክፈታቸውን ተከትሎ በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ ጦርነት እየተካሄደ ነው። ኢራን እየተፈጸመባት ላለው ጥቃት አጸፋውን በቀጣናው ባሉ የአሜሪካ ወዳጅ አገራት ላይ እየፈጸመች ነው። ለዚህ ደግሞ ኢራን ርካሽ እና ውጤታማ የሆኑትን ሻሂድ-136 የተባሉ አጥፍቶ ጠፊ ድሮኖችን በስፋት እየተጠቀመች ነው። ይህ በምሥል እና በቪዲዮ የተደገፈው ዘገባ ስለድሮኖቹ ምንነት ይተነትናል።

ማክሰኞ 24 ማርች 2026 ጥዋት 4:02:11
ኢራን በሕንድ ውቅያኖስ ዲያጎ ጋርሲያ ደሴት ላይ ወደሚገኘው የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) እና የአሜሪካ የጋራ ወታደራዊ ሰፈር ላይ የረዥም ርቀት ባለስቲክ ሚሳዔሎችን ማስወንጨፏ በመካከለኛው ምሥራቅ ያለውን ግጭት እየተባባሰ መምጣቱን ያሳያል። በእርግጥ ሚሳዔሎቹ ወደታቀደላቸው ዒላማ ሳይደርሱ ቀርተዋል። ነገር ግን የእስራኤል የመከላከያ ሠራዊት ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ እንዲህ ዓይነት የረዥም ርቀት ሚሳዔሎች ጥቅም ላይ ሲውሉ ይህ የመጀመሪያው እንደሆነ ተናግሯል።

ሰኞ 21 ሴፕቴምበር 2026 ጥዋት 3:57:11
በአዲስ አበባ የሚገኙ አንዳንድ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች ለአንድ ተማሪ በዓመት ከሚያስከፍሉት ክፍያ አንጻር ከፍተኛ የሚባሉ ዋጋዎችን ያስቀምጣሉ። በአውሮፓውያኑ 2026/27 የትምህርት ዘመን የወጡ የክፍያ መረጃዎች እነዚህ ትምህርት ቤቶች በዓመት እስከ 37 ሺህ ዶላር በላይ ወይም ወደ ስድስት ሚሊዮን የሚጠጋ ብር እንደሚያስከፍሉ ያመለክታሉ። ትምህርት ቤቶቹ እንደ ተማሪው ዜግነት፣ የክፍል ደረጃ እና የክፍያ ዓይነት የተለያየ ተመንም አላቸው።

ሰኞ 10 ኦገስት 2026 ጥዋት 4:05:08
ከጋብቻ በፊት የሚደረገው የሽምግልና ሥነ ሥርዓት ከፍተኛ ድግስ እና ገንዘብ የሚፈስበት እየሆነ መጥቷል። ከሚዘጋጀው ድል ያለ ድግስ ባሻገር በመቶ ሺዎች ብር የሚያስወጡ ቄንጠኛ ግዙፍ የአበባ ‘እቅፎች’ ደግሞ የሽምግልናው ሥርዓት አካል ሆነዋል። በተለይ የሚቀርበው የአበባ ስጦታ መነጋገሪያ ሆኗል። የሽምግልና ሥነ ሥርዓት የሰርግን ቦታ እየተካ ነው? ግዙፉ የአበባ ስጦታስ ከየት የመጣ ልማድ ነው?

ቅዳሜ 1 ኦገስት 2026 ጥዋት 4:56:42
ዲጄ ሲባል መጀመሪያ የሚመጣልን ምሥል ምናልባትም የዳንስ ወለል ላይ ወዝ ወዝ የሚሉ ሰዎች እና ብልጭ ድርግም የሚል መብራት ይሆናል። እነዚህ ዲጄዎች ግን ማንኛውንም ቦታ ለሙዚቃቸው መዳረሻ ማድረግ የሚችሉ ናቸው። ጋራዥ፣ ቴአትር ቤት፣ ፀጉር ቤት፣ መጻሕፍት መደብር፣ ልብስ ሰፊ ቤት፣ ግንባታው ያልተጠናቀቀ 40/60፣ ሸክላ ሠሪ ቤት፣ ወፍጮ ቤት፣ ውይይት ታክሲ. . . የማይገቡበት የለም።

ሰኞ 17 ኦገስት 2026 ጥዋት 3:57:58
አይጦች በጎ ስም የላቸውም፤ ሰዎች ከቤታቸው፣ ምግብ እና የተለያዩ እቃዎች ከሚያስቀምጡባቸው ሥፍራዎች አይጦችን ለማራቅ መርዝ ወይም መጥመድ ይጠቀማሉ። በአጠቃላይ አይጦች ከጥፋት ጋር ስለሚያያዙ በበርካቶች ዘንድ የተጠሉ ናቸው። ኢትዮጵያዊው ሳይንቲስት ምርምር የሚያደርጉባቸው ባለ ፓስፖርት አይጦች ግን ለሰው ልጅ ጤና እና ደኅንነት ከፍተኛ ጥቅም አላቸው።

ቅዳሜ 6 ጁን 2026 ጥዋት 4:22:46
በሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ተገርበው በአዲስ መልክ የተሠሩ ሙዚቃዎች የዩቲዩብ ገፆችን ወርረዋል። የአንጋፋ እና ተወዳጅ ድምጻውያን የሙዚቃ ሥራዎች አማርኛው በተኮላተፈ የኤአይ አንደበት እየተዘፈኑ ነው። አንዳንዶቹ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ዕይታዎች አሏቸው። የአድማጭን ትኩረት የሳቡም ይመስላሉ። ለመሆኑ የዘመኑ የቴክኖሎጂ ልህቀት በተለይ በሙዚቃው ዘርፍ ምን ያሳጣ፣ ምን ያስገኝ ይሆን? የኢትዮጵያን ሙዚቃስ በምን መልኩ ሊለውጠው ይችላል?

እሑድ 9 ኦገስት 2026 ጥዋት 4:57:37
የአዳም ረታ አዲሱ ‘መዝሙረ ሄላም’ የተሰኘው የረዥም ልብ ወለድ መጽሐፍ 1,008 ገጾች ሲኖሩት በአምስት ክፍሎች የተከፈለ ነው። ይህ የአዳም አዲስ መጽሐፍ ከዚህ ቀደም የሚጠቀማቸው እንደ ሕፅናዊነት ያሉ ሥነ ጽሑፋዊ ቴክኒኮችን የያዘ መሆኑን በመጽሐፉ አርትኦት ላይ የተሳተፈው ቢኒያም አቡራ ለቢቢሲ ተናግሯል። የመጽሐፉ መቼት ከዚህ ቀደም እንደነበሩ የደራሲው ሥራዎች ከ1950ዎቹ ማለቂያ እስከ 70ዎቹ መጨረሻ ያሉ ናቸው። መጽሐፉ መጠሪያ የሆነችው ሄላም ከዋና ገጸባሕሪያቱ አንዷ ስትሆን በሁሉም ክፍል ውስጥ ትገኛለች። ለሕፅናዊነት አጻጻፉ ኹነኛ ማስተሳሰሪያ በመሆን ታገለግላለች። ቢቢሲ ከአርታኢው ቢኒያም ጋር ያደረገውን ቆይታ እነሆ. . .

ማክሰኞ 28 ጁላይ 2026 ጥዋት 3:59:29
በኢትዮጵያ ከግማሽ በላይ የሚሆኑ ሴቶች ባል ሚስቱን ለመደብደብ አሳማኝ ምክንያት ይኖረዋል ብለው እንደሚያምኑ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ያደረገው ጥናት አመለከተ። ሚስትን ለመምታት አሳማኝ ምክንያት እንዳለ የሚያስቡ ወንዶች ብዛት ከሴቶች ያነሰ ቢሆንም፤ ከዚህ ቀደም ከነበረው አንጻር በ11 በመቶ ጨምሮ ተገኝቷል።

ዓርብ 11 ሴፕቴምበር 2026 ጥዋት 4:11:34
በዓለም ላይ ያሉ የተለያዩ አገራት ሕዝቦች አዲስ ዓመታቸውን የሚያከብሩት በተለያየ ጊዜ ነው። በርካታ የምዕራባውያን እና ከእነሱ ጋር ትስስር ያላቸው አገራት ጥር ወር ላይ አዲስ ዓመታቸውን የሚጀምሩ ሲሆን፣ አንዳንድ የእስያ አገራት ደግሞ ከዚህ የተለየ የአዲስ ዓመት አከባበር አላቸው። በተለያዩ የዓለማችን ክፍል የሚገኙ አገራት አዲስ ኣመትን እንዴት ያከብሩታል?

ማክሰኞ 1 ሴፕቴምበር 2026 ጥዋት 9:45:18
ባለፓስፖርቶቹ የሰውን በሽታ የሚለዩት አይጦች

ማክሰኞ 1 ሴፕቴምበር 2026 ጥዋት 8:35:24
የቦዲ ቢዩልደሮችን ልብ ቀጥ እያደረገ ያለው ነገር ምንድን ነው?